የድኅረ-ምረቃ ትምህርት የምዝገባ ቀን የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ!

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የ2ኛ(በመደበኛ እና ተከታታይ ት/ት) እና 3ኛ ዲግሪ ትምህርት ፕሮግራሞች አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ቀደም ሲል ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ምዝገባ ማካሄድ ላልቻላችሁ የምዝገባ ቀን ከጥቅምት 27 እስከ ኅዳር 05/2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ በመሆኑ በተጠቀሱት ቀናት በማመልከት መማር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

አመልካቾች፡

  • የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ሰርተፊኬት እና Student Copy ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤li>
  • የማመልከቻ ክፍያ ብር 200.00 በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000258464428 ከፍለው ደረሰኝ ይዘው መቅረብ የምችሉ፡፡
  • የሀገር አቀፍ የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ወስደዉ ማለፊያ ነጥብ ያመጡና የመጀመሪያ ዲግሪ Official Transcript ከተማሩበት ተቋም ማስላክ የሚችሉ፤
  • የማመልከቻ ጊዜ፡

  • ከጥቅምት 27 እስከ ኅዳር 05/2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ በመሆኑ በተጠቀሱት ቀናት በማመልከት መማር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
  • የማመልከቻ ቦታ፡

  •  በዩኒቨርስቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም  በOnline በ https://application.inu.edu.et ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  • የመግቢያ ፈተና፡ ወደፊት በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
    ለበለጠ መረጃ፡ በ058-827-03-40 ይደውሉ፡፡ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት